Welcome to
Home የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሰራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቢሽን ጎበኙ።

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሰራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቢሽን ጎበኙ።

06th November, 2023

ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሰራተኞች የቱሪዝም ሚኒስቴር በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡
በኤግዚቢሽኑ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን የሚያመላክቱ ቅሪተ አካላት፤ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መስህቦችን ሊያስረዳ በሚችል መልኩ በተለያዩ ቅርፆች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ለእይታ ቀርበዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉ የቢሮው ሰራተኞች በሰጡት አስተያየት የሃገራቸውን የቱሪዝም መስህቦች በአንድ ቦታ መመልከታ በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይም ቦታው ድረስ በመሄድ ጉብኝት ለማድረግ ተነሳሽነት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡
.

Copyright © All rights reserved.