Welcome to
Home አፍሪካ በዓለም በኢኖቬስንና ሥራ ፈጠራ መስክ የሚገባትን ቦታ መያዝ አለባት።

አፍሪካ በዓለም በኢኖቬስንና ሥራ ፈጠራ መስክ የሚገባትን ቦታ መያዝ አለባት።

18th September, 2023

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የ2023 ዓለም አቀፍ የስታርትአፕ ሽልማት የአፍሪካ ጉባኤ በሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀምሯል፡፡የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ መድረኩ ከውድድር ባለፈ ኢኖቬተሮችንና ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች የሚገናኙበትና ትስስር የሚፈጥሩበት ነው፡፡ ለኢትዮጵያም በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም በሰፊው ለማሳያየት ዕድል የሚፈጥር ትልቅ መድረክ ነው፡፡ ስለሆነም በሀገራችን ያሉ ስታርትአፖች፣ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችና ቴክኖሎጂስቶች ሰው ሰራሽ ድንበሮችን ተሻግረው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር እየሰራን እንገኛለን፡፡ አብዛኛው ህዝብ ወጣት በሆነባት አፍሪካ ለዓለም ችግር መፍትሄ ማፍለቅ የሚችሉ ስታርትአፖችና ኢንተርፕሪነሮች መገኛ ናት፡፡ ለስታርትአፖች፣ ኢንተርፕሪነሮች እና ለጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ምቹ ሁኔታን መፍጠርና በአህጉሪቱ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ ይቻላል፡፡ስለሆነም አፍሪካ በዓለም በኢኖቬስንና ሥራ ፈጠራ መስክ የሚገባትን ቦታ መያዝ ብለዋል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በበኩላቸው የፈጠራ ሥራ ፈጣሪዎችን ተግዳሮት ለመቅረፍ የተጀመሩ ሀገራዊ ተነሳሽነት እና ሌሎች መርሃ ግብሮችን ሊበረታቱ የሚገባቸው መሆኑን ጠቁመው ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄዱ ለምናልመው አገራዊና አህጉራዊ የኢኮኖሚ እድገት ፋዳው የላቀ ነው ብለዋል፡፡ጉባኤው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጠጡ 70 ስታርታፖች መካከል የመጨረሻ 15ቱ እውቅናና ማበረታቻ ይሰጣቸዋል፡፡ ጉባኤውን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮያ ኢንተርፕሪነርሲ ኢንስቲትዩት እና ከአለም አቀፉ ኢኖቬሽን ኢኒሼቲቭ ግሩፕጋረ በጋራ በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡ 


.

Copyright © All rights reserved.