Welcome to
College የቦሌ ማኑፋክቼሪንግ ኮሌጅ በ2017 ባለፉት ሶስት ወራት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸሙን ገመገመ።

የቦሌ ማኑፋክቼሪንግ ኮሌጅ በ2017 ባለፉት ሶስት ወራት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸሙን ገመገመ።

15th March, 2025

የቦሌ ማኑፋክቼሪንግ ኮሌጅ በ2017 ባለፉት ሶስት ወራት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸሙን ገመገመ።
የቦሌ ማኑፋክቼሪንግ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም የ3 ወራት የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸሙን ገምግሞ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
በውይይቱ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ልመንህ ምህረቱ፣ የቦሌ ማኑፉክቸሪንግ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ታደሰ መኮነን ጨምሮ በርካታ የኮሌጁ ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በኮሌጁ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ ውይይቶችን አካሂደዋል።
በመድረኩ ለውይይት መነሻ በቀረበው ሰነድ
የሰው ሃይል ስምሪት ውጤታማ ለማድረግ የሰው ሃይሉን በአግባቡ መምራት እንደሚያስፈልግ ከአሰራርና አደረጃጀት አንጻር የስትራቴጅክ ማኔጅማንትን፣ቴክኖሎጂን ከመጠቀም አንጻር፣ምቹ የስራ ቦታና ምድረ ጊብ ከመፍጠር አኳያ ፣መልካም አስተዳደርን ከማስፈን፣ከካይዘን ትግበራ ስራዎች፣ብልሹ አሰራርን ከመታገልና ከቲቬት እሳቤዎች አንጻር በርካታ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገልጿል።
በመድረኩ አስተያየታቸውን የሰጡ አካላትም ከህንጻ ግንባታ፣ከሰው ሃይል አቅርቦት፣ ከደይ ኬር፣የመማሪያ ክፍሎች እጥረትና ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ ሃሳብ ሰጥተዋል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ልመንህ ምህረቱ በተፈጥሮው መምህር ፈጣን ፣የሚሰራበት አካባቢ እንዲለወጥ ሃሳቦችን የሚያመነጭና ትግል የሚያደርግ አካል መሆኑን በመገለጽ የተደረገው ሪፎርም ሀገርን ለማስቀጠል የተደረገ መሆኑን ማመን እንደሚገባና ያሉትን ሁኔታዎች አጠናክሮ ማስቀጥል እንደሚያስፈልግ በማውሳት የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ እንደ ኮሌጅ ከአሰራር አንጻር ያን ያክል የጎላ ችግር እንደሌለበት ያሉትም ችግሮች በተደረገው ሪፎርም እንደተስተካከሉ ከደይ ኬር ጋር ተያይዞ የተነሱ ጥያቄዎችም አግባብነት ያላቸው እና መንግስትም ከላይ ጀምሮ በትኩረት እየሰራባቸው ያሉና በቅርቡም ሊፈቱ የሚችሉ መሆናቸውን በማውሳት ከህንጻ ግንባታ ጋር የተነሳው ጥያቄ ግን የአጠቃላይ የአመራሩን ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ በጋራ ተወያይቶ የጋራ ምላሽ ይሰጥበታል ብለዋል።

የቦሌ ማኑፉክቸሪንግ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ታደሰ መኮነን በበኩላቸው
የአመራር ውህደት በመፍጠርና ተቀራርቦ በመስራት የውስጥ አቅምን ተጠቅሞ በራስ አቅም በርካታ ተግባራትን ማሳካት መቻሉን በመግለጽ የክኒክና ሙያ ኮሌጅ በዋናነት የሚቋቋመው ገባያውን መሰረት አድርጎ በመሆኑ አዳዲስ ጸጋዎችን በመለየት የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን መስጠት እንደሚችል ተናግረዋል።
.

Copyright © All rights reserved.