Welcome to AATVETB College
Announcement የሰልጣኞችን የብቃት ማረጋገጫ ምጣኔ ለማሳደግ የሚያስችል አዲስ ሞዴል የምዘና መሣሪያ ሥራ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡፡

የሰልጣኞችን የብቃት ማረጋገጫ ምጣኔ ለማሳደግ የሚያስችል አዲስ ሞዴል የምዘና መሣሪያ ሥራ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡፡

02nd July, 2026

ሰኔ 25/2018 ዓ.ም 
በከተማዋ በሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሚሰጠውን የሥልጠና ጥራት ለማረጋገጥና የሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ምዘና (COC) ውጤት ለማሻሻል የሚያስችል አዲስ ዕቅድ መዘጋጀቱን በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ነጋ አረጋዉ ገለጹ።

ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት የሰልጣኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC) ውጤት ከ50 በመቶ በታች የነበረ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት ከኮሌጆች አመራሮችና ከባለድረሻ አካላት ጋር እቅድን ካስኬድ በማድረግ ይህንን ምጣኔ ወደ 81 በመቶ ከፍ ለማድረግ ታቅዶ በንቅናቄ እየተሰራ ይገኛል።

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ይህንን ተጨባጭ ዕቅድ መሬት ላይ ለማውረድ እና በሀገር አቀፍ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ወቅት የሚታዩትን የሥልጠና ክፍተቶች ለመፍታት የከተማዋ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ከ9ኙ የቅንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች እና ከ15ቱ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጋር በጋራ በመሆን አዲስ አሰራር ዘርግቷል።

በዚህም መሠረት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ"ሞዴል ምዘና" መሣሪያ በቢሮው ተዘጋጅቶ ወደ ኮሌጆች እንዲሰራጭ ተደርጓል። ይህም በ2018 ዓ.ም ሥልጠናቸውን የሚያጠናቅቁ 8,514 ሰልጣኞች በቀጥታ ወደ ሥራው ዓለም ከመሰማራታቸው በፊት አስቀድመው በተቋም ደረጃ እና በሞዴል ምዘናዎች እንዲለማመዱና ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

ባለፉት ወራት በማዕከልና በቢሮ መካከል በተደረገው የተቀናጀ አሰራር የምዘና ጣቢያዎች እጥረት የምዘና መቋረጥና የግብዓት እጥረት ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ የተደረገ ሲሆን ይህም የሰልጣኞችን የመብቃት ምጣኔ ደረጃ በደረጃ ለማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ እያገዘ እንደሚገኝ ከዳይሬክቶሬቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.