Welcome to AATVETB College
Announcement የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የፈጠራ ባለቤቶችን በመደገፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እያፋጠነ ይገኛል።

የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የፈጠራ ባለቤቶችን በመደገፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እያፋጠነ ይገኛል።

11th May, 2026

የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የፈጠራ ባለቤቶችን በመደገፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እያፋጠነ ይገኛል።

ግንቦት  3/2018 ዓ.ም 

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከሥልጠና ባለፈ  የፈጠራ ስራዎችን በማፍለቅና ቴክኖሎጂን ወደ ማህበረሰቡ በማሸጋገር ረገድ የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ይጠበቃል።


ይህንን አገራዊ ተልዕኮ በተግባር እየተረጎሙ ካሉ ተቋማት መካከል የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ተጠቃሽ ነው። ኮሌጁ በተለይም የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች  በመቀበል ሃሳባቸውን ወደ ተግባራዊ ምርት የሚቀይሩበትን የኢንኩቤሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፍ በሰፊው እየሰጠ ይገኛል።


የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲን ዶ/ር ሙሉጌታ አለሙ እንደሚገልጹት ኮሌጁ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ግለሰቦችና ኢንተርፕራይዞች ሃሳባቸውን ይዘው ሲመጡ አስፈላጊውን የወርክሾፕ አገልግሎት የቁሳቁስ ድጋፍና የባለሙያ ምክር በነጻ ያገኛሉ።


ይህ ድጋፍ የሚደረገው የፈጠራ ውጤቶቹ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን የሚፈቱና በተለይም አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችን ምርታማነት የሚያሳድጉ ሲሆኑ ነው።

ዶ/ር ሙሉጌታ አክለውም ኮሌጁ ቴክኖሎጂውን አበልጽጎ ለተጠቃሚው ከማድረስ ባለፈ በኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ ሰልጣኞችና መምህራንም ከእነዚህ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እንዲማሩና የዕውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።


ለዚህ የኮሌጁ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስኬት ህያው ምስክር የሚሆነው ወጣት ሮቤል ተስፋዬ ነው። ወጣት ሮቤል የኮሌጁ ሰልጣኝ ባይሆንም የፈጠራ ሃሳቡን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚረዳ የማምረቻ ቦታና ግብዓት ፍለጋ ወደ ኮሌጁ መምጣቱን ይናገራል።


 ሮቤል ይዞት የመጣው "I-Bites" የተሰኘ ዘመናዊና ስማርት የፈጣን ምግብ መሸጫ ካርት (Smart Cart) ዲዛይን ሲሆን ኮሌጁ ሃሳቡን ተቀብሎ በኢንኩቤሽን ማዕከሉ ውስጥ እንዲሰራ ፈቅዶለታል።


ይህ ዘመናዊ ካርት በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የራሱ የዲጂታል ሽያጭ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ያለውና ምግብ ለማብሰል የሚጠቀመውን ኃይል በጥቅም ላይ ከዋለ  ዘይት የሚያመነጭ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
 
ወጣት ሮቤል እንደሚናገረው የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በቁሳቁስና በቦታ ብቻ ሳይሆን ስራው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለገበያ እንዲበቃ በቴክኒክ ባለሙያዎች ጭምር ደግፎታል። ማምረት የምንፈልገው ነገር አለ፣ ግን ቦታና ማሽን የለንም የሚሉ እንደ እሱ ያሉ ወጣቶች የኮሌጁን በር ማንኳኳት እንዳለባቸውም ጥሪውን ያስተላልፋል።



በአጠቃላይ የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅና የወጣት ሮቤል ቅንጅት እንደሚያሳየው የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የፈጠራ ባለቤቶችንና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት የሚያገናኙ ጠንካራ ድልድዮች መሆናቸውን ነው።

.

Copyright © All rights reserved.