Welcome to
Home ጄነራል ዊንጌት "ከፕሮጀክት ጥገኝነት" ወደ "ራስን መቻል"፤ አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ተጀመረ

ጄነራል ዊንጌት "ከፕሮጀክት ጥገኝነት" ወደ "ራስን መቻል"፤ አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ተጀመረ

09th March, 2026

ጄነራል ዊንጌት "ከፕሮጀክት ጥገኝነት" ወደ "ራስን መቻል"፤ አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ተጀመረ 

       የካቲት 28/2018 ዓ.ም 

መንግስት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍን ለማዘመን፣ ተወዳዳሪ ለማድረግና ብቁ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት በኢኮኖሚው ረገድ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን አዲስ ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። 

ይህንን ፖሊሲ መሬት ለማውረድም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም አዲስ የቴሙሥ ስትራቴጂ አውጥቶ ወደ ተግባር ገብቷል። ይህንን አዲስ እሳቤና አተገባበሩን በተመለከተ፣ በጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለስ ይግዛው ጋር ያደረግነውንና በየክፍሉ የሚቀርበውን ቃለ ምልልስ መሰረት ያደረገ ዘገባ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። 

ክፍል 1፡ የለውጡ መነሻ - ከጥገኝነት ወደ ራስን የመቻል ስትራቴጂ

ጄነራል ዊንጌት ከ"ፕሮጀክት ጥገኝነት" ወደ "ዘላቂ አጋርነት"፤ የ2017 ዓ.ም የቴሙሥ ስትራቴጂ ትግበራ

አዲስ አበባ — የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና (ቴሙሥ) ስትራቴጂ፣ ከተዘረዘሩት ወስጥ አንዱ ተቋማት ከመንግስት በጀትና ከጊዜያዊ የፕሮጀክት ድጋፍ ጥገኝነት ወጥተው በራሳቸው ገቢና አቅም የሚተዳደሩበትን (Financial Autonomy) መንገድ እንዲፈጥሩ ይደነግጋል ። 

የጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ መለስ ይግዛው እንደገለጹት፣ ኮሌጁ ይህንን ስትራቴጂ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የረጅም ጊዜ የዘላቂነት እቅድ ነድፏል። "እስካሁን በፕሮጀክቶች ላይ ተመስርተን የምንሰራበት መንገድ ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ አልነበረም፤ ፕሮጀክቱ ሲያልቅ ስራው አብሮ ይቆማል" የሚሉት አቶ መለስ፣ አዲሱ ስትራቴጂ ግን ወደፊት ከኢንዱስትሪዎች ጋር በዘላቂ "ስትራቴጂያዊ አጋርነት" (Partnership) የምንጓዝበትን መንገድ በግልጽ አስቀምጦልናል ብለዋል።

ኮሌጁ አሁን ባለው የሽግግር ወቅት፣ የፕሮጀክት ድጋፎችን ለጊዜው እንደ መነሻ በመጠቀም፣ በተመሳሳይ ጊዜ የራሱን ገቢ ማመንጫ ስልቶች በማጠናከር ከጥገኝነት ለመውጣት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ዲኑ አክለው ገልጸዋል።

የተመልካቾች ተሳትፎ (Comment Section)፦

ክቡራን ተመልካቾቻችን፤ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከጊዜያዊ የውጭ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ወጥተው በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች አጋርነት ላይ መመሰረታቸው ለስልጠናው ቀጣይነት ምን ያህል ፋይዳ ይኖረዋል? በእርግጥስ ተቋማቱ በራሳቸው እንዲቆሙ ያስችላቸዋል? ሃሳባችሁን በኮመንት አጋሩን! 

.

Copyright © All rights reserved.