Welcome to AATVETB College
Announcement ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፑራቶስ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን የቤከሪ ሙያተኞች በሙሉ የሥራ ዕድል በማረጋገጥ አስመረቀ!!

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፑራቶስ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን የቤከሪ ሙያተኞች በሙሉ የሥራ ዕድል በማረጋገጥ አስመረቀ!!

26th September, 2026

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፑራቶስ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን የቤከሪ ሙያተኞች በሙሉ የሥራ ዕድል በማረጋገጥ አስመረቀ!!

🌼 መስከረም 15/2019 ዓ.ም 🌼

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፑራቶስ (Puratos Bakery School Charity Organisation) ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን 24 የመጀመሪያ ዙር የቤከሪ ሙያ ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

በኬክ፣ ዳቦ እና ቸኮሌት አሰራር የሰለጠኑት እነዚህ ተመራቂዎች የብቃት ማረጋገጫ (COC) ምዘናን ሙሉ በሙሉ ያለፉ ሲሆን የትምህርት ወጪያቸውም ሙሉ በሙሉ በፑራቶስ ተቋም የተሸፈነ መሆኑ ተገልጿል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር አኔሊስ ቨርስቲሼል (Annelies Verstichel)፣ የፑራቶስ ድርጅት መስራችና ሃላፊ ጆል ስግርስ (Jole Segeres)፣ የተለያዩ ድርጅቶች ኃላፊዎች፣ የኮሌጆች አመራሮች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ታዳሚ ሆነዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚዴክሳ ከበደ ከግሉ አልሚ ጋር ቅንጀት ፈጥሮ የዜጎችን ክህሎት ማሳደግ የስራ ዕድልን ማስፋት እና ተዓምራዊ ዕድገትን ማስመዝገብ የሚቻለው በትብብር መሆኑን ይህ መርሐግብር ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ፑራቶስና ጀነራል ዊንጌት አብረው መስራታቸው ከሙያዊ ክህሎትና ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በሌላ በኩል የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው በበኩላቸው ይህ ስልጠና የመንግሥትና የግል ተቋማትን (PPP) አጋርነት በማጠናከር የክህሎት ክፍተቶችን ለማስቀረት ታስቦ የተዘጋጀ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ማሸጋገር ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዋና ዲኑ አክለውም ሰልጣኞቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው ከመመረቃቸው በፊት ሙሉ በሙሉ በካርፉር (Carrefour) ኩባንያ የሥራ ዕድል ማግኘታቸው የትብብሩን ስኬታማነት በጉልህ እንደሚያሳይ አብራርተዋል።

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቀጣይም ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና በመስጠትና የሰልጣኞችን ቁጥር በማሳደግ የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ብቁ ሙያተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.