Welcome to
Home ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአንድ ምዕተ ዓመት ጉዞ በኋላ ወደ ጥንታዊ ስያሜው ሲመለስ የዓለም አቀፍ ጥራት (ISO) የምስክር ወረቀት ባለቤት ሆኗል፡፡

ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአንድ ምዕተ ዓመት ጉዞ በኋላ ወደ ጥንታዊ ስያሜው ሲመለስ የዓለም አቀፍ ጥራት (ISO) የምስክር ወረቀት ባለቤት ሆኗል፡፡

10th February, 2026

ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአንድ ምዕተ ዓመት ጉዞ በኋላ ወደ ጥንታዊ ስያሜው ሲመለስ የዓለም አቀፍ ጥራት (ISO) የምስክር ወረቀት ባለቤት ሆኗል፡፡

 የካቲት 3/2018 ዓ.ም 

በአገራችን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የሆነው አንጋፋው ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል  በልዩ ድምቀት አከበረ።

 ኮሌጁ ይህንን ታሪካዊ ምዕራፍ ሲያከብር ለዓመታት "እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ተብሎ ይጠራበት የነበረውን ስያሜ በመተው ወደ ቀድሞው ታሪካዊ መጠሪያው "ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" በይፋ ተመልሷል።

በተጨማሪም የትምህርት ጥራት አስተዳደር ስርዓቱን ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማድረስ ባደረገው ጥረት የ ISO 21001:2018 (EOMS) የምስክር ወረቀት ባለቤት መሆኑ በበዓሉ ላይ ተበስሯል።

በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ  የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ  የውጤት ተኮር ሥልጠናና ተቋማት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ዳግማዊት ግርማ   የኮሌጁን ታሪካዊ ጉዞ  በማውሳት አድንቀዋል።

 ኮሌጁ  ለአንድ ምዕተ ዓመት የአገሪቱን የኢንዱስትሪ መሪዎችና ባለሙያዎችን ሲያፈራ የኖረ የጥበብ ማዕከልም ነው ያሉት ኃላፊዋ  ስያሜው ወደ ቀድሞው መመለሱ ታሪክን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማገናኘት ትልቅ ፋይዳ እንዳለውና የISO እውቅና ማግኘቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ  ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ዋስትና እንደሚሆን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ተኬ ብርሃነ በበኩላቸው፣ ኮሌጁ የጥራት ፍተሻዎችን አልፎ የISO 21001:2018 ባለቤት መሆኑን አረጋግጠዋል። "ይህ የምስክር ወረቀት ኮሌጁ የሚሰጠው ትምህርትና ስልጠና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን ማረጋገጫ ነው፤ ይህም ለሌሎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አርአያ የሚሆን ተግባር ነው" ሲሉ የጥራት ደረጃውን አስፈላጊነት አስረድተዋል፡፡

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ተወካይ  ዋና ዲን  አቶ ደመላሽ ተስፋዬ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ቀኑ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ድርብ ደስታ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሌጁ ወደ ቀደመ  ስያሜው መለወጡ  ታሪኩን አድሷል በISO የምስክር ወረቀት ደግሞ የወደፊት ጉዞውን በጥራት ላይ እንዲመሰረት አድርጓል ብለዋል። ኮሌጁ በቀጣይም በቴክኖሎጂ ሽግግርና በሰው ኃይል ልማት የአንበሳውን ድርሻ መወጣቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ1917 ዓ.ም ተመስርቶ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ትምህርትና ቴክኖሎጂ በማቀጣጠል ረገድ ትልቅ አሻራ ያረፈበት ተቋም ነው። አሁን ላይ ታሪካዊ ስያሜውንና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን አጣምሮ መያዙ ለቀጣዩ 100 ዓመት አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።

በመርሀ ግብሩ ኮሌጁ ያፈራቸው የጥበብ ባለሙያዎችን ጨምሮ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት አባላት፣የኮሌጅ ዲኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  ተገኝተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.