Welcome to AATVETB College
Announcement ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋም አመራር ሥርዓት ዕውቅና አገኘ።

ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋም አመራር ሥርዓት ዕውቅና አገኘ።

18th July, 2026

 ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም 

በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በትምህርት አሰጣጥና በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ላሳየው የላቀ ጥራት፣ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) የISO 21001:2025 ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋም አመራር ሥርዓት (EOMS) ሰርተፍኬት ባለቤት ሆነ።

በሰርተፍኬት ርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ኮሌጁ ለደረሰበት የጥራት ደረጃ አድናቆታቸውን በመግለጽ ይህ ዕውቅና ቀጣይነት ያለው ጥረት የሚጠይቅ መሆኑንና ተቋሙ ደረጃውን ጠብቆ እንዲቆይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

የኮሌጁ ዋና ዲን ዶ/ር ቢንያም አወቀ በበኩላቸው ስኬቱ የአመራሩ፣ የአሰልጣኞችና የሰልጣኞች የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ጠቅሰው ይህም ለቀጣዩ ትውልድ አርአያ የሚሆን የቴክኒክና ሙያ ተቋም ለመገንባት ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.