Welcome to AATVETB College
Announcement ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምቹና ውብ የስልጠና አካባቢ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምቹና ውብ የስልጠና አካባቢ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

24th June, 2026


🇪🇹 ሰኔ  16/2018 ዓ.ም 🇪🇹

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና የሀገርን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን ወሳኝ ሚና እንዳለው ይታወቃል ይህንን እውነታ የተገነዘበው የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቋሙን ለስልጠናና ለቴክኖሎጂ ፈጠራ ምቹ፣ ጽዱ እና ውብ በማድረግ፣ የሰው ኃይል ምርታማነትን ለማሳደግ  ጥረት እያደረገ ይገኛል።



ኮሌጁ የቴክኒክና ሙያ ልህቀትን ከሀገራዊ የልማት ግቦች ጋር በማጣመር  ግቢውን ለሰልጣኞች፣ ለሰራተኞችና ለማህበረሰቡ ሳቢ የስራና የስልጠና አካባቢ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

በዚህም ኮሌጁ የስልጠና አካባቢን ማሳመር የሰልጣኞችን ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነት እንደሚያሳድግ በመረዳት  በዋናነት የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን   እየሰራ ይገኛል።

በተጨማሪም ሰልጣኞች ከስልጠና ሰዓት ውጭ የሚጠቀሙባቸው የፅሞናና የንባብ ማዕዘናትን ማዘጋጀት እንዲሁም የፅዳት እና የስነ-ስርዓት ባህልን በኮሌጁ እሴቶች ውስጥ ማካተት  የእቅዱ አካል ናቸው።

የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ሸለማ ንጉሱ  እንደሚገልጹት ከሆነ "ምቹ እና አረንጓዴ የስልጠና አካባቢን መፍጠር  የቴክኖሎጂ፣ የሃሳብ ፈጠራ እና ጥራት ያለው ስልጠና መሰረት ነው" ብለዋል።

አያይዘውም ኮሌጁን በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ስታንዳርዱን የማስጠበቅ የላቀ ውጤት የማስመዝገብ ስራ በቁርጠኝነት እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በሂደቱም ኮሌጁ ራሱን በማደስና ዘመናዊ የስልጠና አከባቢን በመፍጠር ሂደት ግንባር ቀደም  ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።



የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እያከናወነ ያለው ይህ ተግባር ተቋሙን ከስልጠና  ማዕከልነት ባለፈ የፈጠራና የብቃት ማማ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። እንደነዚህ ያሉ ተግባራት ተቋማዊ ተወዳዳሪነትን ከመጨመራቸው ባለፈ በሰልጣኞች ዘንድ አዎንታዊ የስራ ባህልን በመገንባት፣ ለሀገሪቱ የሰው ኃይል ግንባታ ጥራት ያለው መሰረት ይጥላሉ።

.

Copyright © All rights reserved.