⚠️ምዝገባው እየተጠናቀቀ ነው!
✅ ሁሉም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አዲስ ሰልጣኞችን እየተቀበሉ ነው! ብዙዎች የቅበላ ጊዜው ሳያልቅ ተመዝግበዋል። እርስዎም ጊዜው ሳያልፍዎ በመደበኛ እና በአጫጭር ስልጠናዎች የሙያ ባለቤት ይሁኑ!
✅ በየትኛው የሙያ መስክ መሰልጠን ይፈልጋሉ? በምህንድስና እና በአይሲቲ፤ በግብና እና በሆቴልና መስተንግዶ፣ በፋሽን ዲዛየን ...ወይስ ለመወሰን ተቸግረዋል? ለመወሰን ከተቸገሩ የሳይኮሜትሪክ ምዘና ጭንቀትዎን ያቀልልዎታል።
✅የሳይኮሜትሪክ ምዘናው በመሻትዎ ብቻ ሣይሆን መክሊትና ባህሪዎን መሰረት በማድረግ ‹‹በየትኛው መስክ ብሰለጥን ውጤታማ እሆናለሁ?›› ለሚለው ጥያቄዎ አስተማማኝ ምላሽን ይሰጥዎታል።
👉 አቅራቢያዎ የሚገኘውን የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን ይጎብኙ! የምዝገባ ቀን ሳይጠናቀቅ ዛሬውኑ ለስኬትዎ ስንቅም ትጥቅም የሚሆኖትን ሙያ መርጠው ይመዝገቡ!
.