Welcome to
Announcement ''ከአንድ ክፍለዘመን ስኬት ወደ ላቀ የልህቀት ማእከልነት'' ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

''ከአንድ ክፍለዘመን ስኬት ወደ ላቀ የልህቀት ማእከልነት'' ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

22nd April, 2026

'ከአንድ ክፍለዘመን ስኬት ወደ ላቀ የልህቀት ማእከልነት'' ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 

አዲስ አበባ | ሚያዝያ 13/ 2018 ዓ.ም

“ ከዜሮ ወደ አንድ"፦ አዲስ ዓለምን የመፍጠር ጥበብ

ወደ ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የለውጥ ጉዞ ከመግባታችን በፊት፣ አንድን ተቋም "ከዜሮ ወደ አንድ" ማሸጋገር ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት። 

በቢዝነስና በፈጠራው ዓለም "ከአንድ ወደ ብዙ" (1 to n) መሄድ ማለት፣ ቀድሞ የነበረን ነገር ማባዛት ወይም ማሻሻል ማለት ነው። ነገር ግን "ከዜሮ ወደ አንድ" (0 to 1) መሸጋገር ማለት፣ ቀድሞ ያልነበረን አዲስ ነገር መፍጠር፣ የታሰረን አሠራር ሰብሮ መውጣትና ተቋሙን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ማሻገር ማለት ነው። ይህ ሽግግር ደግሞ ያለ "የድፍረት እርምጃ" አይታሰብም። የድፍረት እርምጃ ማለት ፍርሃት የሌለበት ጉዞ ሳይሆን፣ ተቋማዊ ለውጥን ለማምጣት ሲባል የቆየን የለመዱትን አሠራር (Status Quo) ለመቀየር የሚወሰን ቆራጥ ውሳኔ ነው። 

የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ፋና ወጊ የሆነው ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ (TMS)፤ ጥንታዊ ታሪኩን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማሰናሰል "ከዜሮ ወደ አንድ" የተሸጋገረበትን የሪፎርም ጉዞ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ገለጹ።

ኮሌጁ በአዲሱ የዘርፉ መሪ እሳቤዎች (11 DNAs) አማካኝነት ተቋሙን ከቀድሞው የባህል አሠራር አውጥቶ ወደ ዲጂታልና ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሸጋገር የወሰዳቸው የድፍረት እርምጃዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን ተመልክቷል። 

ዋና ዲኑ አቶ ተሾመ ፈይሳ የኮሌጁን ስልታዊ ለውጥ እንደሚከተለው ይተነትኑታል፦ 

1. የብራንዲንግ DNA፦ የታሪክ አሻራን የመመለስ ድፍረት

ተቋሙን "ከዜሮ ወደ አንድ" ካደረጉት እርምጃዎች አንዱ የብራንዲንግ ጉዳይ ነው። ተቋሙ "እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ" በሚል ስያሜ ለዓመታት ቢቆይም፣ ታሪካዊ ማንነቱ ግን "ተፈሪ መኮንን" ከሚለው ስም ጋር የተቆራኘ ነበር። 

"የብራንዲንግ DNA ትልቁ ግብ ለዘርፉ ያለውን የተንሸዋረረ አመለካከት መቀየር ነው" የሚሉት አቶ ተሾመ፤ ኮሌጁ በአዋጅ ቁጥር 131/2017 ታሪካዊ ስያሜውን መልሶ እንዲያገኝ መጠየቁና ማጽናቱ፣ ተቋሙን ወደ ቀድሞ ዝናው የመለሰ ትልቅ የድፍረት ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል። 

2. የጥራት DNA፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ (ISO) መመዘን

አንድን አንጋፋ ተቋም በዓለም አቀፍ መመዘኛ እንዲመዘን መፍቀድ ትልቅ ድፍረት ይጠይቃል። ኮሌጁ የትምህርት ሥርዓቱን ስታንዳርዳይዝ ለማድረግ በ ISO 21001:2018 ሰርተፋይ መሆኑ፣ አሠራሩን ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ የጥራት ቁጥጥር ያሸጋገረ "ከዜሮ ወደ አንድ" የመሄድ ማሳያ ነው። 

3. የዲጂታላይዜሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር

ኮሌጁ ከመንግሥት በጀት ተረጅነት ወጥቶ የራሱን ገቢ የሚያመነጭበትን የ"ኢንተርፕራይዝ" አሠራር በህጋዊ መንገድ አቋቁሟል። ከዚህ በተጨማሪ፦ 

የዲጂታል መሰረተ ልማት፦ በዓለም ባንክ (EASA Project) ድጋፍ በ80 ሚሊዮን ብር ወጪ መላው የኮሌጁ ግቢ በገመድ አልባ ኢንተርኔት (Wireless) ተሸፍኗል። ይህም ለBlended Learning እና ለe-service አሠራር መሠረት ጥሏል። 

ሰልጣኞች የቴክኖሎጂውን እገዛ (AI supportive elements) በመጠቀም ጥበብና ቴክኖሎጂን አቀናጅተው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ ተቋሙን ወደ ኢንዱስትሪ 5.0 ሽግግር እያዘጋጀው መሆኑን ዲኑ አስረድተዋል። 

4. የአሠራር ልህቀት በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን

በቀድሞው አሠራር በቁጥር ብቻ ይገለጹ የነበሩ ኢንተርፕራይዞች፣ አሁን በ LMS (Labor Management System) አማካኝነት በዲጂታል እንዲመዘገቡ ተደርጓል። ይህ አሠራር የሌሉትን አሉ ከማለት ይልቅ፣ ያሉትን ሪሶርሶች በጥራትና በተጨባጭ ለውጥ ላይ አተኩሮ ለመደገፍ ያስቻለ ሽግግር ነው። 

የክፍል አንድ ማጠቃለያ፦

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባለፈው አንድ ክፍለ ዘመን የነበረውን የታሪክ ትስስር ሳይለቅ፣ በአዲሱ ሪፎርም የታገዘ ዘመናዊና ቴክኖሎጂ መር ተቋም ሆኖ ለመቀጠል የጀመረው ጉዞ "ከዜሮ ወደ አንድ" የመሸጋገር ትልቅ የድፍረት ምሳሌ ነው። 

.

Copyright © All rights reserved.