Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ስደተኞችን ተጠቃሚ በሚያደርግ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት የአሰራር ጋይድላይን ላይ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ስደተኞችን ተጠቃሚ በሚያደርግ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት የአሰራር ጋይድላይን ላይ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
05th July, 2025
የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ስደተኞችን ተጠቃሚ በሚያደርግ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት የአሰራር ጋይድላይን ላይ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
ሰኔ 26/2017 ዓ. ም
ስልጠናው በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የተካሄደ ሲሆን የማዕከል፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ የሴፍቲኔት አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ ስደተኞችን በሴፍትኔት ተጠቃሚ ማድረግ/ራይዘን/ላይ ትኩረቱን ያደረ ነው።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሞላ እንደገለጹት ስደኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወነ ባለው ስራ መንግስትና የአለም ባንክ በጋራ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች፣ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ስለስደተኞች ተጠቃሚነት/ራይዞን/ ያገኙትን ግንዛቤ በመተግበር ስደተኞች በአካባቢ ልማት ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ብለዋል።
የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በ1ለ5 እና በ1 ለ30 የተደራጁ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰለሞን ለፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች የስራ ቦታን የመለየትና አምራች እንዲሆኑ ለማስቻል ኃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል በማለት ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስደተኞች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት/ራይዞን/ላይ ለባለሙያዎች ግንዛቤ መፈጠሩ የተጀመረውን የስራ ዕድል ፈጠራ ውጤታማ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ ለሚሳተፉ ተጠቃሚዎች የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች እንደሚሟሉም ተገልጿል።
.