Welcome to
College በ2017 በጀት ዓመት ከ38 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አስታወቀ

በ2017 በጀት ዓመት ከ38 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አስታወቀ

05th July, 2025

በ2017 በጀት ዓመት ከ38 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አስታወቀ
በ2017 በጀት ዓመት ከ38 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ስራ መፍጠር መቻሉን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት አመታዊ የስራ አፈጻጸሙን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው የስራ ግምገማ አስታውቋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም አመታዊ አፈጻጸሙን ከተቋሙ ቁልፍ ተግባራት፣የኢኒሸቲብ፣ቅንጅታዊ አሰራርና ከመልካም አስተዳደር ስራዎች ጋር ተያይዞ ያከናወናቸውን ተግባራት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጥንካሬና በክፍተት ገምግሞ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላትም የእውቅና ሰርተፊኬት ሰጥቷል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጸ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ በቅርቡ ሪፎርም ካደረጉ ተቋማት አንዱ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት መሆኑን በማውሳት በበጀት ዓመቱ ጽ/ቤቱና የጽ/ቤቱ ስራዎች ከወረዳ እስከ ክ/ከተማ በተሻለ ና በተቀናጀ የስራ አመራር ሂደት መመራታቸውንና በአብዛኞቹ ስራዎች የተሻለ ውጤት መመዝገቡን በመጠቆም በበጀት ዓመቱ የነበሩ ቅንጅታዊ አሰራሮችንና የነበራቸውን አጠቃላይ ፋይዳ በተመለከተ ማብራሪያ በመስጠት የተሰሩ ስራዎች አጠቃላይ ስኬት የሚለካው ምን ያህል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ አደረግን በሚለው መስፈርት መሆኑንና ሁሉም አካል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግና ተቋሙን ወደ ላቀ የስኬት ማማ ለማሳደግ ያሉ ክፍተቶችን በቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ ውስጥ አካቶ ጥንካሬዎችን ደግሞ ይበልጥ አዳብሮ በማስቀጠል የተቀናጀ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቤዛ ደመቀ ለውይይቱ ባቀረቡት የመነሻ ሰነድ ከመልካም አስተዳደር ተግባራት ፣አሰሪና ሰራተኛን የሚያሳትፍ ወጥ መደላድል ከመፍጠር፣ ከአገልግሎት አሰጣጥና ከሪፎርም ስራዎች፣ ቅሬታና አቤቱታን ከመፍታት፣ብልሹ አሰራርን ከመታገል፣የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ከማሳለጥ።፣ከአቅም ግንባታ ስራዎች፣ከስራ ስምሪትና የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ፣ከስራ እድል ፈጠራ፣ከአማራጭ የጸጋ ልየታ፣የአሰሪና ሰራተኛ ግንዛቤን ከማሳደግ ጋርና ሌሎችም አሰራሮች ጋር ተያይዞ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያና ትንታኔ ሰጥተዋል።
በበጀት ዓመቱ በአብዛኞቹ የጽ/ቤቱ ተግባራት የላቀ ስኬት መመዝገቡንና የግንዛቤ ፈጠራ ላይ በስፋት መሰራቱን ብሎም ከ38 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የመፍጠር ስራ መሰራቱን የገለጹት ወ/ሮ ቤዛ በቀጣይ 90 ቀናት ንቅናቄና በቀጣይ በጀት ዓመት መደበኛ የስራ ጊዜም ቅጥር ላይ የበለጠ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበትም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የተሻለ የስራ አፈጻጸም ብቃት ላሳዩ ወረዳዎች፣ተቋማትና ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
.

Copyright © All rights reserved.