Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
More
Support
Submit Ticket
My Tickets
Service
About
Contact Us
Status
Login
Announcement
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኞችን የመብቃት ምጣኔ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂክ መፍትሄ ማፈላለግ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ።
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኞችን የመብቃት ምጣኔ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂክ መፍትሄ ማፈላለግ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ።
16th August, 2025
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኞችን የመብቃት ምጣኔ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂክ መፍትሄ ማፈላለግ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ።
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሰልጣኞችን የመብቃት ምጣኔ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂክ መፍትሄ ማፈላለግ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
ይህ
የተገለፀው የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተጠሪ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይትና የሐምሌ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ባካሄዱበት ወቅት ነው።
በመድረኩ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት ልማት ዘርፍና የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የሐምሌ ወር ዕቅድ አፈፃፀም እንዲሁም የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዕቅድና ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
በተያዘው የ2018 በጀት በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ስድስት ግቦች 24 ዓላማዎች እንዲሁም 92 ተግባራት መለየታቸው በመድረኩ ተመላክቷል።
በ2017 በጀት ዓመት ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ የመደበኛ ሰልጣኞች ውስጥ ዝቅተኛ አፈፃፀም መመዝገቡ የተገለፀ ሲሆን አጭር ጊዜ ሰልጣኞች የመብቃት ምጣኔ 95 በመቶ ማድረስ ተችሏል።
ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ 23ሺ 351 ልል ክህሎት እና 4ሺ208 ክህሎት መር የአጭር ጊዜ ስልጠና መስጠት መቻሉ ተነስቷል።
የአሰልጣኞች አቅም ከማሳደግ አንፃር ለ196 አሰልጣኞች ፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በሐምሌ ወር ውስጥ ከተመዘኑ 437 አሰልጣኞች ውስጥ 340 የሚሆኑት ብቁ ሆነዋል።
አካባቢያዊ የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆችን በዞን በመለየት የተጀመረው የዲፈረንሼሽን ተግባር ወደ ተግባር ምዕራፍ መቃረቡ ተገልጿል።
አሰራሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመደገፍ በተያዘው ዕቅድ መሰረት የE-scool ሲስተምን ጥቅም ላይ በማዋል ሂደት ተግባራዊ እንቅስቄሴ
ተጀምሯል።
በዚህም በየኮሌጁ የሚያስተዳድሩት ባለሙያዎችን ከመወከል ባለፈ ሰልጣኞችን በየሴክሽን የመለየት እና ውጤት የማስገባት ስራ ተጀምሯል ።
በሌላ በኩል 13ሺ 369 ኢንተርፕራይዞች ለመደገፍ የልየታ ስራ የተሰራ ሲሆን ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ በ2017 በጀት ዓመት የተቀዱ ቴክኖሎጂዎች ወደ ማህበረሰቡ ለማስፋት በተጀመረው ተግባር 25 ቴክኖሎጂዎችን የመለየት ስራ መሰራቱ ተጠቁሟል።
የውይይት መድረኩ በተያዘው በጀት ዓመት በታቀደው ልክ ተግባራት ስለመፈፀማቸው በመፈተሽ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የሰልጣኞችን የመብቃት ምጣኔ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂክ መፍትሄ ማፈላለግ ላይ አመራሩ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።
ክቡር አቶ ጥራቱ አያይዘውም በበጀት ዓመቱ ለማምጣት የታሰበው ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ እንደሚያስፈልግም ጨምረው ገልፀዋል።
ለዚህ ደግሞ የአመራር ውህደት ወሳኝ ሚና እንዳለው በመረዳት ከኮሌጅ ማህበረሰብ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በዕቅዶቹ ዙሪያ የጋራ መግባባትን በመፍጠር ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ብለዋል።
በቀጣይ ጊዜያትም የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አመራሮች የግምገማ መድረክ እንዲሁም ዞኒንግና ዲፈረንሼሽን በመተግበር የአሰልጣኞች ምደባ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
.