Welcome to
College የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የጀመሩትን የሪፎርም ስራ አጠናክረው በማስቀጠል ብቁና ተወዳዳሪ ተቋም ሊሆኑ እንደሚባ ተገለፀ።

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የጀመሩትን የሪፎርም ስራ አጠናክረው በማስቀጠል ብቁና ተወዳዳሪ ተቋም ሊሆኑ እንደሚባ ተገለፀ።

15th March, 2025

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የጀመሩትን የሪፎርም ስራ አጠናክረው በማስቀጠል ብቁና ተወዳዳሪ ተቋም ሊሆኑ እንደሚባ ተገለፀ።
መጋቢት 05/2017 ዓ ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሥሩ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አፈፃፀም ደረጃ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በኮሌጅ ደረጃ በተካሄደው ግምገማ የተጀመረውን የሪፎርም ሥራ አጠናክሮ ከማስቀጠል አንፃር ኮሌጆች ባለፉት ሦስት ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት አቅርበዋል። የኮሌጆች ሪፖርት ከቀረበ በኋላ በቢሮ ደረጃ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ወይይቱን የቢሮው የዘርፍ አመራሮች፣ አማካሪዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲመሩት ተደርጓል።
በአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የተካሄደውን ውይይት የመሩት በቢሮው የውጤት ተኮር ስልጠና እና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አበራ ብሩ የግምገማ መድረኩ በሁሉም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንደተካሄደ ገልፀው የውይይቱ ዋና አላማ የሪፎርም ስራው በኮሌጅ ደረጃ ያለበትን ደረጃ በመገምገም በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ መሆኑን ገልፀዋል።
ዶ/ር አበራ አያይዘውም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከአገር አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ተቋም ለመሆን የጀመሩትን የሪፎርም ስራ አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል።
.

Copyright © All rights reserved.