Welcome to
College የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሠራተኞች "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሠራተኞች "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ።

15th March, 2025

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሠራተኞች "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ።
መጋቢት 5 /2017 ዓ.ም
በክብረ-በዓሉ የቢሮው ሴት ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ49ኛ ጊዜ አየተከበረ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ አመጣጡ እና ፋይዳውን የተመለከተ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
''March 8'' ቀደምት እናቶቻችን እና እህቶቻችን በመጨቆናቸው እና በመገለላቸው ምክንያት አድሎና ጭቆና የወለደው በዓል ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘለቃሽ ባህሩ ተናግረዋል።
ጽሕፈት ቤት ኃላፊዋ አክለውም በአሉን ስናከብር መንግስት ባመቻቸልን እድል በመጠቀም እና በማህበራዊ፣በኢኮኖሚያዊ እና በፓለቲካዊ ዘርፍ በንቃት በመሳተፍ የሀገራችን የብልፅግና ጉዞ ማፋጠን ይገባል ብለዋል።
በማህበረሰቡ ዘንድ ለሴቶች ያለው አመለካከት የታዛባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምርታማነታችን እንዲቀንስ አድርጓል ያሉት ደግሞ የቢሮው የኑሮ ማሻሻያ ቡድን መሪ እና የስርዓተ ፆታ ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ኢዶሳ ናቸው።
ይህን የተዛባ የስዓተ ፆታ አመለካከት በማረም እና የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሁሉን አቀፍ ለውጥ ማስመዝገብ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
እንደ ስራና ክህሎት ቢሮ የሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ከመድረክ ተጠቁሟል።
አለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን እ.ኤ.አ በ1911 ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሴቶችና ወንዶች በተገኙበት በአራት ሀገራት የተከበረ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሴቶች ከወንዶች እኩል በኢንዱስትሪው ውስጥ ቢቀጠሩም በሰሩት ልክ ክፍያ ባለማግኘታቸው እ.ኤ.አ 1908 የተሻሻለ ደመወዝ ክፍያ እና የመመረጥ መብት እንዲከበር አደባባይ በመውጣታቸው March 8 ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ሆኖ እንዲከበር ምክንያት ሆኗል ተብሏል ።
The staff of Addis Ab
.

Copyright © All rights reserved.