Welcome to
Announcement በተፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆን በስራቸው ጥሩ ውጤት እያመጡ መሆኑን ወጣቶች ገለፁ።

በተፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆን በስራቸው ጥሩ ውጤት እያመጡ መሆኑን ወጣቶች ገለፁ።

16th August, 2025

በተፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆን በስራቸው ጥሩ ውጤት እያመጡ መሆኑን ወጣቶች ገለፁ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሀሴ 03/2017 ዓ.ም
በክፍለ ከተማው ወረዳ 06 አስተዳደር የስራ እድል ፈጠራን የ90 ቀናት እቅድ አካል በማድረግ ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል መፍጠር ችሏል።
ከስራ እድሉ ተጠቃሚ ከሆኑት ወጣቶች መካከል አንዱ የሆነው አቶ ሱራፌል፣ እሱና አራቱ ጓደኞቹ "ሱራፌል፣ ራሄልና ጓደኞቻቸው" በሚል ስያሜ የቆዳ ውጤቶችን በማምረት ኢንተርፕራይዝ ማቋቋማቸውን ተናግሯል።
ከዚህ በፊት ስራ ፈላጊ እንደነበሩ የገለፀው ወጣት ሱራፌል፣ አሁን ግን በተለይ ደግሞ የወረዳው አስተዳደር በፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ በመሆናቸው በስራቸው ጥሩ ውጤት እያመጡ መሆኑን አስረድቷል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ90 ቀናት የስራ ዕቅድ ውስጥ ከተካተቱ 18 የትኩረት ነጥቦች አንዱ ለወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠር ላይ ትልቅ ትኩረት በማድረግ የስራ አጥነትን በመቀነስ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
.

Copyright © All rights reserved.