Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በከተማዋ ያለውን የስራ ዕድል ፀጋ በጥናት በመለየት የስራ ዕድል ፈጠራውን በላቀ ደረጃ ለመፈፀም በሚያስችል ጥናት ላይ ስልጠና ተሰጠ።
በከተማዋ ያለውን የስራ ዕድል ፀጋ በጥናት በመለየት የስራ ዕድል ፈጠራውን በላቀ ደረጃ ለመፈፀም በሚያስችል ጥናት ላይ ስልጠና ተሰጠ።
28th June, 2025
በከተማዋ ያለውን የስራ ዕድል ፀጋ በጥናት በመለየት የስራ ዕድል ፈጠራውን በላቀ ደረጃ ለመፈፀም በሚያስችል ጥናት ላይ ስልጠና ተሰጠ።
ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጠናው የፀጋ ልየታ አሰራር ጋይድላይን እና የስራ ዕድል መፍጠሪያ መስኮች ጥናት ላይ ከወረዳ እስከ ማዕከል ለሚገኙ የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው መክፈቻ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ጥናቱ በከተማዋ ያለውን የስራ ዕድል ፀጋ በጥናት በመለየት ከዚህ ቀደም ሲፈጠሩ ከነበሩ የስራ ዕድሎች በላቀ ሁኔታ ለከተማዋ ነዋሪዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።
ስልጠናው በስራ ዕድል መፍጠሪያ ጋይድ ላይን ላይ ግልፅነት በመፍጠር የዘርፉ አመራርና ባለሙያ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጥ ያስችላል ሲሉም ክቡር አቶ ጥራቱ ጨምረው ገልጸዋል።
ጥናቱ ከተለመደው አካሄድ ወጣ በማለት ንዑሳን ዘርፎች ባካተተ መልኩ ጥቅም ላይ በማዋል የ2018 እና 2019 በጀት ዓመት የስራ ዕድሎችን በመተንበይ ረገድ መስፈንጠሪያ እንደሚሆንም አብራርተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አማካኝነት የተጠናው ጥናት በዋናነት ለፀጋ ምንነት ብያኔ በመስጠት የፀጋ ልየታ መስፈርቶች ፤የስራ ዕድል ፈጠራ የዳሳ ጥናት፤የሀገራት ተሞክሮ እንዲሁም ምክረ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
በተመሳሳይ የስራ ዕድል መፍጠሪያ ንዑሳን ዘርፎች ዝርዝር ቀርቦ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ጥናቱ በስራ ዕድል ፈጠራ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ነቅሶ በማውጣት ለቀጣይ ስራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል።
ቢሮው በስራ ዕድል ፈጠራ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ከትራንስፎርሜሽናል ዕቅዱ በተቀዳ መሰረት አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም የስራ አጥ ምጣኔውን ወደ ነጠላ አሀዝ በማውረድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የቢሮው ዘርፍ ኃላፊዎች ተናግረዋል።
.