Welcome to AATVETB College
Announcement የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቋል

የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቋል

07th September, 2026

ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቋል

​ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም - “የእመርታ ቀን”ን በማስመልከት ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ማዕቀፍ ስር ለሚደግፋቸው ኢንተርፕራይዞች በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ። ኮሌጁ ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎችን ወደ ማህበረሰቡ እና አምራቹ ዘርፍ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

​የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን ወ/ሮ አስናቀች መንግስቱ እንደገለጹት፣ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፡-

​የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ፦ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን (ቴክኒካል ክህሎት፣ ካይዘን፣ እና ኢንተርፕረነርሺፕ) በመጠቀም በ5ቱ እድገት ተኮር ዘርፎች ለሚገኙ 1,084 አዲስ እና ነባር ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ 1.5 ሚሊዮን ብር ሃብት ማፍራት ተችሏል።

​የሙያ ብቃት ምዘና፦ የአንቀሳቃሾችን የሙያ ብቃት ምዘና የመብቃት ምጣኔ 73 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ፣ ከተመዘኑት አንቀሳቃሾች መካከል ሁሉንም ማሳለፍ በመቻሉ 100 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል።

​ሞዴል ኢንተርፕራይዞች፦ በተደረገው ርብርብ 24 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን ማፍራት ተችሏል።

​የቴክኖሎጂ ሽግግር፦ በዳሰሳ ጥናት 22 ቴክኖሎጂዎች ተለይተው፣ 9 አዋጭ ቴክኖሎጂዎች በመቀዳት ለተመረጡ ኢንተርፕራይዞች ተሸጋግረዋል። በዚህም ከተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች 710,000 ብር ሃብት ለማፍራት ታቅዶ 645,035.12 ብር (90.85%) ማግኘት ተችሏል።

​ኮሌጁ አሁን ላይ አዲሱን የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ስኬታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባለፈው ዓመት ያጋጠሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ላይ ሰፊ ምክክር አድርጓል። በቀጣዩ ዓመት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፉን ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ እመርታ ለማስመሰል እንደሚሰራ ተመላክቷል።

.

Copyright © All rights reserved.