የምስራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኝ ቃልኪዳን ኢትዮጵያን ወክላ በቻይና የጸጉርና ሜካፕ ውድድር ላይ ድንቅ ብቃቷን እያሳየች ትገኛለች።
🌼 መስከረም 15/2018 ዓ.ም 🌼
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የምስራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኝ ቃልኪዳን ኢትዮጵያን ወክላ በቻይና የጸጉርና ሜካፕ ውድድር ላይ ድንቅ ብቃቷን እያሳየች ይገኛል፡፡
የምሥራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የደረጃ 4 የጸጉርና ሜካፕ ጥበብ ዘርፍ ሰልጣኝ የሆነችው ቃልኪዳን ፈንታሁን በቻይና ሀገር እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የወጣቶች ሙያ ውድድር ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክላ ድንቅ የፈጠራ ክህሎቷን ለአለም እያስተዋወቀች ይገኛል።
ይህም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍየተሰማሩ ወጣቶች በተግባራዊ እውቀታቸውና በሙያዊ ብቃታቸው ያስመሰከረ ነው፡፡ ቃልኪዳን አሁን ለደረሰችበት የውድድር መድረክ ያበቃት በተግባር ትምህርቷ ላይ ባሳየችው ከፍተኛ ትጋት፣ ፍላጎትና የላቀ ብቃት ነው። ሰልጣኟ ከዚህ ቀደም፡ በኮሌጅ ደረጃ በተካሄደው የክህሎት ውድድር 1ኛ፤ በክላስተር ደረጃ በተደረገው ውድድር 1ኛ፤በከተማ ደረጃ በተካሄደው ከፍተኛ የክህሎት ማሳያ ውድድር ላይም እንዲሁ 1ኛ በመውጣት አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል።
እነዚህን አገር አቀፍ የደረጃ ውድድሮች በአሸናፊነት በማጠናቀቅ የጀመረችውን የስኬት ጉዞ፣ አሁን ላይ ሀገረ በቻይና በሚካሄደው አለም አቀፍ መድረክ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል እንድትሳተፍ መነሻ ሆኗታል።
ይህ የቃልኪዳን ተሳትፎ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በትክክለኛ ትጋትና ጥረት ከተከናወነ እስከ አለም አቀፍ ደረጃ ሊያደርስ የሚችል ታላቅ የሙያ መንገድ መሆኑን ያስመሰከረ ነው።
በተጨማሪም ለሁሉም የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች "በትጋት ከተሰራ የማይደረስበት የስኬት ማማ የለም" የሚል ትልቅ ተስፋና ማበረታቻ የሚሰጥ፣ በተግባር የተረጋገጠ አርአያነት ያለው አሻራ ነው።ይህ ውድድር ወጣቶች ያላቸውን የተግባርና ሙያዊ ክህሎት ለአለም የሚያስተዋውቁበት ታላቅ መድረክ ሲሆን፣ የቃልኪዳን ተሳትፎ የሀገራችንን ሙያተኞች አቅምና የትምህርት ጥራት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በግልጽ የሚያስመሰክር ነው።
ቃልኪዳን በያዘችው የፈጠራ ጥበብ፣ በጽናቷና በሙያዊ ብቃቷ ሀገራችንን በኮከብነት እንደምታስጠራ ሙሉ እምነት አለን።
ለሰልጣኛችን ቃልኪዳን መልካም እድልና ታላቅ ስኬት እንመኛለን!
.