Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ዜጎች ስራ ሳያማርጡ በከተማዋ ባሉ የስራ ዕድል ፀጋዎች ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የአመለካከት ቀረፃ ስራው ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
ዜጎች ስራ ሳያማርጡ በከተማዋ ባሉ የስራ ዕድል ፀጋዎች ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የአመለካከት ቀረፃ ስራው ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
09th May, 2025
ዜጎች ስራ ሳያማርጡ በከተማዋ ባሉ የስራ ዕድል ፀጋዎች ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የአመለካከት ቀረፃ ስራው ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።
ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በ55 ቀናት የሥራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ተወያይቶ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል ።
በውይይቱ በንቅናቄው የተከናወኑ አበይት ተግባራት የቀረቡ ሲሆን በዚህም ከስራ ፈላጊ ምዝገባ አንፃር ከዕቅድ በላይ የተፈፀመ መሆኑን እና በስራ ዕድል ፈጠራ ለወጣቶች እና ቤተሰቦቻቸው ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆኑ ተጠቁሟል።
በበጀት ዓመቱ የ55 ቀናት የንቅናቄ ስራዎችን ጨምሮ 301ሺ767 ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ እና የዕቅዱን 101 በመቶ ማሳካት መቻሉ የተገለፀ ሲሆን 17ሺ249 ኢንተርፕራይዞች መመዝገብ መቻሉን እና 10ሺ801 አዲስ ኢንተርፕራይዞች ማደራጀት መቻሉ ተመላክቷል።
በውይይቱ የ55 ቀናት የንቅናቄ ስራዎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ የዜጎች የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እና ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ስልጠናቸውን እንዲከታተሉ ከማድረግ አንፃር እንዲሁም የዶሮ ቺፕስ ስራ ቦታ ልየታ የደረሰበት ደረጃ እና ስራውን በፍጥነት መጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ ዜጎች ስራ ሳያማርጡ በከተማዋ ባሉ የስራ ዕድል ፀጋዎች ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የአመለካከት ቀረፃ ስራው ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዜያት በዕቅድ ከተያዙት በተለይም ኢንተርፕራይዞችን በE-LMIS ከመመገብ አንፃር ስራውን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ብሩህ የንግድ ፈጠራ ሀሳብ እና ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ከአለማማጅ ድርጅቶች ጋር በቅርበት መስራት እደሚያስፈልግ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በውይይቱ የክፍለ ከተሞች ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና ስራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ምክትል ጽሕፈት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
.