Welcome to AATVETB College
Announcement ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።

ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።

06th August, 2026

 ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም 



በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የስልጠና ጥራቱን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ዘመናዊ የመሰረተ ልማት እና የስልጠና ወርክሾፓችን በዛሬው ዕለት በድምቀት አስመረቀ።

በዚሁ ታላቅ መርሐ ግብር ለምረቃ ከበቁት መካከል ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የተገነቡ እና በዘመኑ የሲሙሌተር (Simulator) እንዲሁም የቪዥዋል ሪያሊቲ (Visual Reality) ቴክኖሎጂዎች የተደራጁ ስማርት የማሰልጠኛ ክፍሎች ዋነኞቹ ናቸው።


እነዚህ መሰረተ ልማቶች ሰልጣኞች በተግባር የተደገፈና ዘመኑን የዋጀ ክህሎት እንዲጨብጡ በማስቻል ለስራው አለም ብቁ እና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።


ከዚህ በተጨማሪም ለአሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ የስፖርት ሜዳ እንዲሁም የኮሌጁን ፍላጎት አሟልቶ ለአካባቢው ነዋሪዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ የሚያደርግ የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓድ ተቆፍሮ ለምረቃ በቅቷል።

በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደን ጨምሮ የኮሌጁ ዋና ዲን ቢንያም አወቀ (ዶ/ር) ፣የክፍለ ከተማዉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሚ ሙሄ አሊ፣ የክፍለ ከተማዉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቦጋለች ተድላ፣ የክፍለ ከተማዉ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮሌጁ ማህበረሰብ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኮሌጁ ዋና ዲን በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተቋሙ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ የስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፣ የተገነቡት የመሰረተ ልማት አውታሮች ለኮሌጁ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው ነዋሪዎችም ዘላቂ ጠቀሜታ እንዲሰጡ በጥንቃቄ ሊያዙ እንደሚገባ አሳስበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.