Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በተጠሪ ተቋማቱ ለሚያካሂደው ድጋፍና ክትትል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በተጠሪ ተቋማቱ ለሚያካሂደው ድጋፍና ክትትል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
24th May, 2025
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በተጠሪ ተቋማቱ ለሚያካሂደው ድጋፍና ክትትል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
ግንቦት 13/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በክፍለ ከተማ እና ወረዳ ስራና ክህሎት ጽሕፈት ቤቶች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ከነገ ጀምሮ ለሚያካሂደው ድጋፍና ክትትል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን ተከትሎ በስራው ለሚሳተፉ ጄኔራሊስት ቡድን አባላት ኦረንቴሽን ሰጥቷል፡፡
በኦረንቴሽኑ የድጋፍና ክትትሉ አጠቃላይ ዓላማ አስፈላጊነት አንዲሁም ስልቱን በተመለከ ለአባላቱ ገለፃ ተደርጓል፡፡
ድጋፍና ክትትሉ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ተይዘው የተከናወኑ ተግባራትን በማረጋገጥ እና ያልተከናወኑ ተግባራትን በመለየት ሁሉም ተግባራቱን እስከ ግንቦት መጨረሻ እንዲጠናቀቅ የማድረግ ዓላማ እንዳለው በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ ተናግረዋል፡፡
ቢሮው ከተቋቋመበት ተልዕኮ አንፃር በተጠሪ ተቋማቱ በዕቅድ የተያዙ ተግባራት በምንያህል ደረጃ እንደተፈጸሙ በመፈተሸ፤ተግባራቱ ትርጉም ባለው መንገድ የህብረተሰቡን ህይወት ስለመለወጣቸው የሚረጋገጥበት እና ልምድ የሚሆኑ ተግባራት ለቀጣይ በጀት ዓመት ግብዓት የሚሆኑበት ዕድል እደሚፈጥር ተጠቁሟል፡፡
ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ በቢሮው በአራቱ ዘርፎች በተጠሪ ተቋማቱ ያላቸውን አፈፃፀም በውይየት፤በምልከታ እና በሰነድ ፍተሻ ስልቶች እያረጋገጠ እንደሚሄድ ተገልጿል፡፡
.