Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
ሪፎርም በተደረጉ ኮሌጆች የመጡ ለውጦች እና በቀጣይ ትኩረት ተደርጉ በሚሰራባቸው ጉዳዩች ዙሪያ የጋራ ምክክር ተደረገ::
ሪፎርም በተደረጉ ኮሌጆች የመጡ ለውጦች እና በቀጣይ ትኩረት ተደርጉ በሚሰራባቸው ጉዳዩች ዙሪያ የጋራ ምክክር ተደረገ::
15th March, 2025
ሪፎርም በተደረጉ ኮሌጆች የመጡ ለውጦች እና በቀጣይ ትኩረት ተደርጉ በሚሰራባቸው ጉዳዩች ዙሪያ የጋራ ምክክር ተደረገ::
መጋቢት 5/2017ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ
እንዳልካቸው አስራት ሪፎርም በተደረጉ ኮሌጆች በመጡ ለውጦች እና በቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዩች ዙሪያ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር ተወያይተዋል።
የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የወጣቶችን ስራ አጥነት ለመቅረፍ እና የኢንዱስትሪውን ምርታማነት ለማሳደግ አስተዎፆ እያበረከተ እንደሚገኝ አቶ እንዳልካቸው አስራት ገልፀው የበቃ ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለገበያ በማቅረብ፣ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ በማሸጋገር እና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት በዘርፉ በርካታ ስራዎች ማከናወን ተችሏል ብለዋል።
የኮሌጆች ሪፎርም ስራ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ በተከናወኑ ተግባራት ምን ተጨባጭ ለውጦችና ውጤቶች እንደመጡ እና ከማን ምን ይጠበቃል የሚል ሀሳብ ተነስቶ ተወያይተዋል።
ያልተሻገርናቸው ምን ክፍተቶች እንዳሉ ከእያንዳንዱ ኮሌጅ ማህበረሰብ ጋር በመወያየት እና መግባባት በመፍጠር የተሻሉ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና የሚታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ እርምት በመውሰድ ሪፎርሙን በላቀ ውጤት ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በመነሻ ሰነዱ ተዳሷል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በተሟላ የሪፎርም ሂደት ውስጥ እንዲያልፍ በአስራር፣ አደረጃጀት፣ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሀይል ያሉ ማነቆዎችን ተለይተው ለመፍታት በትኩረት እየተሰራበት መሆኑንም በውይይቱ ተነስቷል።
ሪፎርም በማድረግ ብዝሀነትን ካካተተና ውህደት ያለው አመራር በመፍጠር በኮሌጆች ውስጥ የስራ መነቃቃትና ተነሳሽነት መፍጠር እንደሚቻል፣ የቴክኖሎጂ ማሸጋገር፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት እና ሰልጥነው በተሻለ ሁኔታ ለመስራት የአሰልጣኞችን ተነሳሽነት ከፍ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ምድረ ግቢን፣ ቢሮዎችንና የስልጠና ወርክ ሾፖችን ለተገልጋይና ለአገልጋዩ ምቹ የማድረግ ስራ መሰራት መቻሉ የሪፎርሙ ውጤት መሆኑ ተገልፆል።
በቀጣይም በኮሌጆች የለሙ የመረጃ ስርዓት በሙሉ አቅም ወደ ተግባር ማስገባት፣ የተሟላ የሰልጣኝ፣ የአሰልጣኝ፣ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን እና ኢንተርፕራይዞች መረጃ ማደራጀት፣ በ2017 ዓ.ም ስልጠናቸውን የሚያጠናቅቁ መደበኛ ሰልጣኞች ከወዲሁ በማብቃት ሙያዊ ብቃታቸው በሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ እንዲረጋገጥ ማድረግ የሚሉት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
.