Welcome to
College የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር መስራት የሚያስችለው ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር መስራት የሚያስችለው ስምምነት ተፈራረመ፡፡

28th June, 2025

ቢሮው ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር መስራት የሚያስችለው ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር መስራት የሚያስችለው ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል፡፡
ቢሮው ‹‹የሚሰሩ እጆች ወግ›› በሚል ርዕስ በየ15 ቀኑ ለሚሰራጭ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ነው የስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት ያካሄደው፡፡
በስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ባደረጉት ንግግር ፕሮግራሙ እንደ ሀገር የጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ የዜጎችን አመለካከት በመቀየር ጠንካራ የስራ ባህል የተላበሰ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡
ሚዲያው ካለው ተደራሽነት አንፃር ፕሮግራሙ አውንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የጠቆሙት ክቡር አቶ ጥራቱ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ስራውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚያስችል ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በበኩላቸው የሁለቱ ተቋማት ዋና ዓላማ የትውልድ ግንባታ በመሆኑ ፕሮግራሙ ለትውልድ የሚሻገር ስራ ለመስራት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
ፕሮግራሙ የሚዲያውን ተመራጭነት በማሳደግ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ እንደሚያስችል የተገለጹ ሲሆን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች በማስፋት ለሌሎች የሚዲያ ተቋማት አርዓያ የሚሆን ፕሮግራም እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡
‹‹የሚሰሩ እጆች ወግ›› የተለያዩ የውይይት አጀንዳዎችን እየተቀረጹለት እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ ስራ ያለውን የአመለካከት ዝንፈት በማረም ጠንካራ የስራ ባህል ለማስረጽ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
.

Copyright © All rights reserved.