Welcome to
College በከተማ ደረጃ የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን የማጠቃለያ ምዕራፍ ስራዎች አፈፃፀም ሱፐር ቪዥን ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ሰጠ፡፡

በከተማ ደረጃ የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን የማጠቃለያ ምዕራፍ ስራዎች አፈፃፀም ሱፐር ቪዥን ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ሰጠ፡፡

05th July, 2025

በከተማ ደረጃ የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን የማጠቃለያ ምዕራፍ ስራዎች አፈፃፀም ሱፐር ቪዥን ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ሰጠ፡፡
ሰኔ 23/ 2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረ የሱፐር ቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች የማጠቃለያ ምዕራፍ ዕቅድ አፈፃፀም ሱፐር ቪዥን ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ሰጥቷል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ ለቀናት በቢሮው እና በተመረጡ የዘርፉ መዋቅሮች በሰነድ ፍተሻ እና በመስክ ምልከታ ሲያካሂድ የቆየውን ሱፐርቪዥን በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ከቢሮው ማኔጅመንት አባላት ጋር የመውጫ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ቢሮው የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አቅዶ በየደረጃው ከማውረድ አንስቶ አፈፃፀሙን ለመለካት በየጊዜዉ ያካሄዳቸው የኦዲት ስራዎች አበረታች መሆኑ ተነስቷል።
ስራዎችን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ አንፃርም በተለይም የኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ስርአት ላይ ኢንተርፕራይዞች የመመዝገብ ስራ መሰራቱ እና የአንድ መስኮት አገልግሎት ለማጠናከር የግብአት ስርጭት መደረጉን ቡድኑ አድንቋል።
ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር መተግበሩ የሚበረታታ መሆኑን የጠቀሰው ቡድኑ ተጠያቂነት እያሰፈኑ ከመሄድ አንፃር በትኩረት እንዲሰራ አሳስቧል።
ከመልካም ተሞክሮ አንፃር ሊሰፉ የሚገቡ ሶስት መልካም ተግባራት ማስፋት እንደሚገባም በዚህ ወቅት ተገልጿል።
በሌላ በኩል የፓርቲ ስራዎችን በማጠናከር ሂደት ካለው የሰራተኛ ቁጥር አንፃር የአባላት ቁጥር ከመጨመር አንፃር ትኩረት የሚያስፈልገው መሆኑ የተነሳ ሲሆን ሞዴል ህብረትና ቤተሰብ መፍጠር እንደሚገባም ቡድኑ አስገንዝቧል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ ተግባራቱን በትኩረት መመልከቱን ያደነቁት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የተነሱት ሀሳብና አስተያየቶች ተገቢነት ያላቸው በመሆኑ ለቀጣይ ስራዎች በግብአትነት በመውሰድ የዕቅድ አካል አድርጎ ይሰራል ብለዋል።
.

Copyright © All rights reserved.