Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
"የበቃ አሰልጣኝ፣ክህሎት የጨበጠ ወጣት፣ለሀገር ብልፅግና!" በሚል መሪ ሀሳብ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አመራሮችና አሰልጣኞች ጋር ሲካሄድ የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ።
"የበቃ አሰልጣኝ፣ክህሎት የጨበጠ ወጣት፣ለሀገር ብልፅግና!" በሚል መሪ ሀሳብ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አመራሮችና አሰልጣኞች ጋር ሲካሄድ የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ።
21st May, 2025
"የበቃ አሰልጣኝ፣ክህሎት የጨበጠ ወጣት፣ለሀገር ብልፅግና!" በሚል መሪ ሀሳብ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አመራሮችና አሰልጣኞች ጋር ሲካሄድ የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ።
ግንቦት 10/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ "የበቃ አሰልጣኝ፣ክህሎት የጨበጠ ወጣት፣ለሀገር ብልፅግና!" በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው ውይይት ተጠናቋል።
በውይይቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ከማዕከል በቀረበው ገለፃ መነሻነት የውይይቱ ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየታቸውን ተሰጥተዋል።
የለውጡ መንግስት ስልጣን ተረክቦ ሀገር ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ በፓለቲካ፤በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የትናንቱ በማረም፤ዛሬን በላቀ ትጋት በመከወን ለትውልድ የሚሻገር ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
በከተማችን አዲስ አበባ ሁሉንም ዜጋ ባማከለ መልኩ ከትናንሽ መንደሮች የተጀመረው ሰው ተኮር ተግባራት እንቅስቃሴ አድጎ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ዕውን ማድረግ ያልተለመደ ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች ይህም 24/7 የስራ ባህልን በማስተዋወቅ የስራ ትጋት እንዲጨምር አስችሏል ብለዋል።
የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን በማላቅ ለሀገራዊ ዕድገቱ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የተካሄደው ሪፎርም አበረታች መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎቹ የታለመለት ዓላማ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ጠቁመዋል።
ወቅታዊ የኑሮ ውድነቱን ተከትሎ እየደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ በመንግስት የተወሰዱ የገበያ ማረጋጊያ እርምጃዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የገጠሙ ተግዳሮቶችን በድል ለመወጣት በሚደረገው ጥረት መንግስት የዘርፉን ችግሮች በመለየት እዲፈታ የጠየቁት ተሳታፊዎቹ በቀጣይ ሀገራዊ ብልፅግናውን ለማሳካት እና ዘርፉን ትራንስፎርም ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የውይይት መድረኮቹን የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የኮሌጅ ዲኖች የመሩ ሲሆን ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች እንደየ ኮሌጆቹ ተጨባጭ ሁኔታ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አመራሮችና አሰልጣኞች ውይይት በቀጣይ በከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የውይይት መድረክ ተሳታፊዎች ልየታ ተካሂዷል።
በውይይቱ ለቢሮው ተጠሪ በሆኑ 15 ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና አንድ የልህቀት ማዕከል ላይ የሚገኙ ከ2ሺ919 በላይ አሰልጣኞች ተሳትፈዋል።
.